80 በመቶ የአማራ ክልል አካባቢዎች ለወባ በሽታ ስርጭት ምቹ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

156

ባሕርዳር፡ ጥቅምት 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) በአማራ ክልል ከጥቅምት 10 እስከ 27/2013 ዓ.ም የወባ መከላከል ሳምንት ይከበራል። በሳምንቱ የወባ ሥርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን የተመለከተ ውይይት በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ 80 በመቶ የሚሆኑት የአማራ ክልል አካባቢዎች ለወባ በሽታ ስርጭት ምቹ መሆናቸው ተነስቷል። ወደ 68 በመቶ የሚሆነው የክልሉ ሕዝብም ለወባ በሽታ ተጋላጭ እንደሚሆን ተመላክቷል።

በ2012 ዓ.ም የክልሉ የወባ ስርጭት በ2011 በጀት ዓመት ከነበረው የ66 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ተጠቅሷል። በተያዘው ዓመት ባለፉት ሦስት ወራት የወባ ስርጭት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የአራት በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የወባ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችል ግብዓት እጥረት እንዳጋጠመ ተገልጿል። ባለፉት ስድስት ሳምንታት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የወባ ሥርጭት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩም በውይይቱ ተጠቅሷል።

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃውን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleፕሬዝዳንት ትራምፕ ሱዳንን ከሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ ሊያስወጡ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
Next articleለእንቦጭ አረም መስፋፋት ወደ ሐይቁ የሚገቡ በካይና ደለል የተሸከሙ ፍሳሾች ምክንያት መሆናቸውን የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡