
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 06/2013 ዓ.ም (አብመድ) የዓለም ጤና ድርጅት ፀረ- ቫይረስ መድኃኒት የተባለውን ሬምዴስቬርን ጨምሮ በአራት መድኃኒቶች ላይ ሙከራ አካሂዷል፡፡ መድኃኒቱ ታካሚዎች በሕክምና ተቋማት ውስጥ የሚያሳልፉትን ጊዜ በማሳጠርም ሆነ በሕይወት እንዲቆዩ የሚያበረክቱት አስተዋፅዖ ዝቅተኛ ነው፡፡
ሙከራው ከተደረገባቸው ዉስጥ ሬምዴስቬር፣ ሀይድሮክክሎሮኪን፣ ሎፒናቪርና ኢንተርፌሮን ናቸው፡፡ በሙከራ የተገነው ውጤት በጤናው መስክ ላይ በተሰማሩ ባለሙያዎች የሚገመገም ይሆናል፡፡
በጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ጁሊ ፊሸር (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ለአልጀዚራ እንደተናገሩት የሙከራው ውጤት የሚያበሳጭ ነው፡፡ ሙከራው የሬምዴስቬር ጠቀሜታን በዝርዝር ያላስቀመጠ ነው ብለዋል፡፡
ሬምዴስቬር በኢቦላ ቫይረስ ለተያዙ ሰዎች ተሻሽሎ የተዘጋጀ መድኃኒት ነው፡፡ በአሜሪካው መድኃኒት አምራች ኩባንያ ጊሊያድ የቀረበ ነው፡፡
በኮሮና ቫይረስ ለሚሰቃዩ ሰዎች ሕክምና ለመስጠት ያገለግላል ተብሎ በግንባር ቀደምትነት ጥቅም ላይም ውሏል፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ በተያዙበት ወቅት ይህን መድኃኒት መውሰዳቸውም የሚታወስ ነው፡፡
በኪሩቤል ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
