
ዶክተር ድረስ ሳኀሉ ጎሹ የትምህርት ዝግጅታቸው
• በዲፕሎማ በደን ሳይንስ ከወንዶ ገነት የደን ሳይንስ ኮሌጅ
• የመጀመሪያ ዲግሪ በመልክዓምድርና አካባቢ ጥናት ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ
• የሁለተኛ ዲግሪ በመልካም አስተዳደርና በአመራር ጥበብ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
• የሦስተኛ ዲግሪያቸውን በሥራ አመራር ፍልስፍና ቻይና ሀገር ከሚገኘው ኋጁንግ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡ ዶክተር ድረስ ሳኀሉ ሁሉንም የትምህርት ደረጃዎች በከፍተኛ ማዕረግ ያጠናቀቁ መሆናቸውን ታሪካቸው ያስረዳል፡፡
ዶክተር ድረስ ሳኀሉ በሥራ ልምድ በኩል ደግሞ
• በምስራቅ ጎጃም ዞን በደባይ ጥላት ግን እና በባሶ ሊበን ወረዳ የደን አግሮ ፎረስተሪና የመሬት አስተዳደር ባለሙያ በመሆን ለአራት ዓመታት አገልግለዋል፡፡
• በምስራቅ ጎጃም ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ የአስተዳደር እና ግብርና ጽኅፈት ቤት ኃላፊ በመሆን
• በአነደድ ወረዳ የግብርና ኃላፊ፣ የመሬት አስተዳደር ጽኅፈት ቤት ኃላፊ፣ የሕዝብ ተሣትፎና አደረጃጃት አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡
• በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ ምክትል አስተዳደሪና ግብርና ጽኅፈት ቤት ኃላፊ
• በጃቢ ጠህናን ወረዳ የመሬት አስተዳደር ጽኅፈት ቤት ኃላፊና የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡
• የምዕራብ ጎጃም ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ፣ የሕዝብ ግንኙነትና የከተማ አደረጃት አማካሪ
• በአማራ ክልል የምሁራን ተሳትፎና አደረጃጀት ዘርፍ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡
በታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
