ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መሪዎች ጋር ተወያዩ።

281

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 06/2013 ዓ.ም (አብመድ) ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) ከአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች መሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

ከአማራ እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የክልል መሥተዳድሮች እንዲሁም ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በመተከል ዞን የተፈጸሙ ጥቃቶችን አስመልክቶ ነው የተወያዩት። “ያሉትን ችግሮች ፈትሸን፣ የአካባቢውን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል” ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ በማኀበራዊ ገጻቸው::

Previous articleበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተፈጸሙ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ 504 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
Next articleከተማ አስተዳደሩ በፕላንና በህጋዊ የከተማ እድገት አቅጣጫ ብቻ እንድትማራ አጥብቀው እንደሚሰሩ ዶክተር ድረስ ሳህሉ ተናገሩ።