በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተፈጸሙ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ 504 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

231

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 06/2013ዓ.ም (አብመድ) የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን አስመልክቶ መግለጫ እየሰጠ ነው። በመግለጫውም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተፈጠረው ጥቃት ጋር በተያያዘ 504 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ በማጣራት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ሁከት እና ብጥብጥ 8 ሺህ 666 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው በ4 ሺህ 249 በተያያዘም በ4 ሺህ 249ኙ ላይ ማስረጃ እንደተገኘባቸውም ገልጿል።

በነበሩ ሁከት እና ብጥብጦች 4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙም ተመላክቷል።

በተለያዩ የተደራጁ ከባድ ወንጀሎች ሲፈለጉ የነበሩ ግለሰቦች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር 96 ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉም ታውቋል።

ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን

Previous articleከተማ አስተዳደሩ ዶክተር ድረስ ሳኅሉ ጎሹን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾመ።
Next articleጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መሪዎች ጋር ተወያዩ።