
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 06/2013 ዓ.ም (አብመድ) አሜሪካ በዓለም አቀፉ የልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን አማካይነት በኦሮሚያ ክልል ለሚካሄደው የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ፕሮጀክት ለቴክኒካል ልማት የሚውል የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጋለች።
የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ 50 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንደሚኖረው ኢብኮ ዘግቧል።
ከአዲስ አበባ በ100 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ፕሮጀክት የሚለማው ቲኤም በሚባል የጂኦተርማል ኦፕሬሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ነው።
ዓለም አቀፉ የልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅም ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ በጂኦተርማል፣ በፀሐይ፣ በውኃ እና በንፋስ ኃይል እምቅ አቅም እንዳላት ይታወቃል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
