
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 04/2013ዓ.ም (አብመድ) ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ እያደረጉት ባለው ሦስተኛ ቀን የሥራ ጉብኝት በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ አስጎብኝነት የእንጦጦ ፓርክን በመጎብኘት ላይ ናቸው።
ኢብኮ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዚህ ሳምንት የተመረቀውን የእንጦጦ ፓርክን ፕሮጀክቱ ከመጀመሩ በፊት፣ ፕሮጀክቱ በመሠራት ላይ እያለ እና የአሁኑን የተጠናቀቀውን የፓርክ ጉብኝት ጨምሮ ለሦስት ጊዜ ጎብኝተውታል።
የእንጦጦ ፓርክ ለአንድ ዓመት ያህል ግንባታው ሲካሄድ ቆይቶ መስከረም 30 ቀን 2013ዓ.ም በጠቅላይ ሚነስትር ዐብይ አህመድ ተመርቆ ለሕዝብ ክፍት መደረጉ ይታወሳል።
ሁለቱ መሪዎች ባለፉት ሁለት ቀናትም የኮይሻ እና የታላቁ ሕዳሴ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
