
ፖርቱጋላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በኮሮናቫይረስ መያዙን የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
የጁቬንቱስና ፖርቱጋል አጥቂው በኮሮናቫይረስ መያዙንና የሕመም ምልክቶች ግን እንዳልታዩበት የፖርቱጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ባለፈው እሑድ በአውሮፓ ሀገራት ዋንጫ ማጣሪያ ከፈረንሳይ ያለግብ አቻ የተለያየችው ፖርቱጋል የፊታችን ረቡዕ ከስዊድን ጋር ለሚኖራት ጨዋታ የኮከቧን ግልጋሎት እንደማታገኝ ታውቋል፡፡
