በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ 80 ሺህ ሐሰተኛ ብር ተያዘ፡፡

709

ባሕር ዳር፡ መስከረም 29/2013ዓ.ም (አብመድ) በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በአሽፋ ባህራ ደረዋ ቀበሌ ሐሰተኛ 80 ሺህ ባለአንድ መቶ የብር ኖት የያዘ እጅ ከፈንጅ ተይዞ በቁጥጥር ስር እንደዋለ የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ንጉሴ ዓለሙ እንደገለፁት የእንጅባራ ነዋሪ የሆኑት አቶ ያረጋል ጥላሁን እና አቶ ግርማው ታፈረ ትናንት መስከረም 28/2013 ዓ.ም ከቀኑ 12፡00 አሽፋ ገበያ ሐሰተኛ ብር ይዘው ሲንቀሳቀሱ እንደተገኙ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ወቅት አንድ ግለሰብ ከ15 ሺህ ብር በላይ ይዞ መገበያየት ስለማይቻል እነርሱ የሚገዙት ዕቃ 80 ሺህ ብር ስለሆነባቸው ‘‘በእጅ እንስጥ’’ በማለት በባጃጅ ወጥተው ከመንገድ እንደተቀባበሉት ገልጸዋል፡፡

60 ሺህ ብሩ ወዲያውኑ የተያዘ ሲሆን 20 ሺህ ብሩ ግን ዛሬ መስከረም 29/2013 ዓ.ም አቶ ሙሉቀን አለነ የተባለ ደላላ አምጥቶ ማስረከቡ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ ባለ100 ብር ኖት 80 ሺህ ብር የተያዘ መሆኑን የገለጹት ኢንስፔክተር ንጉሤ የተያዙት ሁለት ግለሰቦች ላይ ምርመራ እያደረጉ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሁሉም ሰው አዲስ የተቀየረውን የብር ኖት እንዳይጭበረበር በደንብ አውቆ መገበያየት እንዳለበትም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፡- የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Previous articleሐሰተኛ የብር ኖቶችን ለመከላከል በትኩረት እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
Next articleሐይቁ በመሙላቱ ወደውጭ የተገፋው የእምቦጭ አረም ተመልሶ እንዳይገባ የሰው ኃይል ሊሠማራ ነው፡፡