በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩ ባለሙያዎች ሀጋራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጅት እንዲያደርጉ ተጠየቀ፡፡

186

ባሕር ዳር፡ መስከረም 29/2013ዓ.ም (አብመድ) በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለሰባት ወራት የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማገዝ ከዚህ ቀደም በመምህርነት ሙያ ሲያገለግሉ የነበሩ መምህራን በአቅራቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለማገልገል ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር መደበኛ ትምህርትን በሚያስቀጥልበት ወቅት በትምህርት ቤቶች አካላዊ ርቀትን ለማስጠበቅ የተማሪዎች ቁጥር ከ20-25 እንዲሆን መወሰኑን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እንደየአካባቢያቸው ሁኔታ በፈረቃ ትምህርት የሚሰጡ ይሆናል፡፡

በዚህም ወቅት በትምህርት ቤቶች የመምህራን እጥረት እንዳይኖር ለማድረግ ከዚህ ቀደም በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩና የመምህርነት ስልጠናን ወሰደው ሌላ ዘርፍ የተቀላቀሉ ባለሙያዎች በየአካባቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶክተር) “እኔም አስተምራለው” በሚል መሪ ሐሳብ ከሰኞ ጀምሮ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ከዚህ ቀደም በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩና በመምህርነት ሙያ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን የመመዝገብ ሥራ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

በዚህም መሠረት ባለሙያዎች በአቅራቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች በመሄድ እና በመመዝገብ የትምህርቱን ዘርፍ በሙያቸው እንዲያግዙ ሚኒስትሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የትምህርት ሚኒስቴር በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Previous articleየሰቆጣ ቃል ኪዳን በ2022ዓ.ም የሕጻናት መቀንጨርን ዜሮ ለማድረግ ጠንክሮ እንደሚሠራ አስታወቀ፡፡
Next articleበጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ፡፡