ሥርዓትን ሳይሆን ሕዝብን ማገልገል የሚችል፣ ዘመናዊና ዘመን ተሻጋሪ ፖሊስን መገንባት የሚያስችል የኢፌዴሪ ፖሊስ ዶክተትሪን ይፋ ተደረገ።

163

ዶክትሪኑ ላለፉት ሁለት ዓመታት በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና በሰላም ሚንስቴር ሲዘጋጅ የቆየ ነው። ዶክትሪኑ ይፋ በተደረገበት ጊዜ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዳሻው ጣሰው ዶክትሪኑ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና በሰላም ሚንስቴር አማካኝነት ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲዘጋጅ የቆየ መሆኑን አስታውቀዋል።

ዶክትሪኑ ይስተዋሉ የነበሩ የፖሊስ ድክመቶች ለመፍታት፣ የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥ፣ የሕዝብ ሰላም እና ደኅንነት ለመጠበቅ የሚችል ዘመናዊና ዘመን ተሻጋሪ ፖሊስን ለመገንባት የሚያስችል እንደሆነም ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል።

የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እንደተናገሩት ደግሞ ፖሊስ የሕዝብ ሰላም እና ደኅንነት ጠባቂ አካል መሆኑን በተግባር ማረጋገጥ፣ ለሥርዓት ሳይሆን ለሕዝብ የሚያገለግል፣ ከፖለቲካ ነፃ የሆነ ሥርዓት ሲቀያየር የማይናወጥ ለሕዝብ የወገነ ፖሊስ መገንባት መሠረታዊ የለውጡ አንድ አካል በመሆኑ ዶክትሪኑ ተዘጋጅቷል። ፖሊስ በሕዝብ የሚፈራ ሳይሆን የሚፈለግ እንዲሆን ዶክትሪኑ ማስፈለጉንም ወይዘሮ ሙፈሪያት ገልጸዋል።

ዶክትሪኑ የሚገነባው ፖሊስ ሙያዊ ብቃትን፣ ታማኝነትን፣ ብዝኃነትንና ሰብዓዊነትን የሚያከብር መሆን እንዳለበትም ያትታል። የፖሊስ ሥራ ውጤታማ ለማድረግም የነቃ የሕዝብ ተሳትፎን ማሳደግ የግድ እንደሆነም ሚኒስትሯ አብራርተዋል።

ዘጋቢ፦ በለጠ ታረቀኝ -ከአዲስ አበባ

ፎቶ:ጌትነት ገደፋው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየኮሮናቫይረስ ስርጭት እየጨመረ ሲሄድ በተቃራኒው የሚጓዘው የማኅበረሰቡ መዘናጋት እንዳሳሰበው የክልሉ ጤሮ ቢሮ አስታወቀ።
Next articleጥንቅሽ ቁረጡ እና ምጠጡ!