የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

1061

ባሕር ዳር፡ መስከረም 28/2013ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፤ በተጨማሪ የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለፕሮጀክቱ መስጠታቸው ተገልጿል፡፡

የአብቁተ ዋና ሥራ አስፈጻሚው መኮንን የለውምወሰን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተቋሙ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የሚውል 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ የአበቁተ የሥራ ኃላፊዎችም ፕሮጀክቱን ለመደገፍ የወር ደመወዛቸውን መስጠታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

አብቁተ ከተሰማራበት የፋይናንስ አገልግሎት በተጨማሪ መሰል ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎችን በመደገፍ ረገድ ተሳትፎ እያደረገ እንደሆነ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

ራሱን ወደ ባንክነት ለማሳደግ በሂደት ላይ ያለው አብቁተ በቀጣይም መሰል ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሰራ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየበርሃ አንበጣው ወደ አማራ ክልል ከፍተኛ ቦታዎች እና ወደ ሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ስርጭቱን ሊያሰፋ እንደሚችል የምሥራቅ አፍሪካ የበርሃ አንበጣ መቆጣጠሪያና መከላከያ ድርጅት አሳሰበ፡፡
Next articleበበረሃ አንበጣ መንጋ በሰብላቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎች እንዲደገፉ ተጠየቀ፡፡