መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ለግድቡ ከ500 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡

211

ባሕር ዳር፡ መስከረም 28/2013ዓ.ም (አብመድ) መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የመንፈስ ልጆቻቸውን በማስተባበር 545 ሺህ ብር ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ በስጦታ ድጋፍ አደረጉ።

መልአከ መንክራት ግርማ ‘‘የዓባይ ወንዝ አምላክ የሰጠን ትልቅ ስጦታ በመሆኑ ለዘመናት ከተኛንበት ተነስተን በዓባይ ላይ ያገባደድነውን ግድብ ለማጠናቀቅ ኢትዮጵያውያን ከመቼውም ጊዜ በላይ መተባበር አለብን’’ ብለዋል።

ከግድቡም ሌላ 645 ሺህ ብር ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ማዋላቸውንና ለግድቡ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መምህር ግርማ መግለጻቸውን ኢ.ፕ.ድ ዘግቧል።

ድጋፉን የተቀበሉት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ድጋፍ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር እና የጽሕፈት ቤቱ ተወካይ ወይዘሮ ፍቅርህ ታምር ለግድቡ ላደረጉት ድጋፍ አመሥግነዋል፡፡ መምህር ግርማም ሆኑ ሌሎችም መንፈሳዊ አባቶች ግድቡን ለማጠናቀቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ መደገፍ እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article297 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዐረቢያ ተመለሱ፡፡
Next articleባንክ በሌለባቸው አካባቢዎች ብሔራዊ ባንክ በሄሊኮፕተር ጭምር ታግዞ አዲሱን የብር ኖት እንዲያቀርብ እየተነጋገረ እንደሚገኝ አብቁተ አስታወቀ፡፡