
ባሕር ዳር፡ መስከረም 28/2013ዓ.ም (አብመድ) የበርሃ አንበጣ መንጋ በምሥራቅ አማራ አካባቢዎች ከተከሰተ ቆይቷል፡፡ መንጋው ከተከሰተበት መስከረም 6/2013 ዓ.ም ጀምሮ በየአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮች፣ የግብርና ባለሙያዎች እና በየደረጃው ያሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ስርጭቱን ለመቆጣጠር ባህላዊ እና ዘመናዊ መንገዶችን እየተጠቀሙ ቢሆንም በበርካታ አካባቢዎች ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ መምጣቱን ተመልክተናል፡፡
ዛሬ በጠዋት በተገኘንበት በሰሜን ወሎ ዞን ሐብሩ ወረዳ ቀበሌ 27 አካባቢ በጠዋት በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት ሲካሄድ አርፍዷል፡፡ ነገር ግን በአካባቢው መልካ ምድራዊ አቀማመጥ እና ሰው በሚኖርባቸው ቦታዎች ለርጭት ምቹ ያልሆኑ አካባቢዎች ላይ መንጋው ሰፍሮ በሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡
በሐብሩ ወረዳ በ13 ቀበሌዎች የአንበጣ መንጋው ተከስቷል፤ በሦስት ቀበሌዎች ላይ ያለ ሰብል ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው- ከሰሜን ወሎ ሀብሩ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m