
ባሕር ዳር፡ መስከረም 28/2013ዓ.ም (አብመድ) በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ደሴ እና ባሕር ዳር ከተሞች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡
በደሴ እየተካሄደ ባለው ውይይት ላይ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ነብዩ ስሁል ሚካኤል እና የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ዴኤታ ሙሉ ነጋ (ዶክተር) ተገኝተዋል፡፡
ተመሳሳይ ዓላማ ያለው ውይይት በባሕር ዳር ከተማም እየተካሄደ ነው፡፡ በባሕር ዳር እየተካሄደ ባለው ውይይት የትግራይ ተወላጆች፣ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ከአዲስ አበባ የመጡ እንግዶች እየተሳተፉ ነው፡፡
የውይይቱ ዓላማ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ እውነታ መረዳት እና መግባባት ላይ መድረስ እንደሆነ በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡ ለውይይቶቹ የመነሻ ሰነዶች በጽሑፍ ተዘጋጅተው ቀርበዋል፡፡
ስለኢሕአዴግ ውህደት፣ ስለውህደቱ አስፈላጊነት፣ የህውኃት ከውህደቱ ማፈንገጥ፣ ህወሀት አሁን ያለበት ሁኔታ እና ስለ አፍራሽ እንቅስቃሴው፣ የብልፅግና ፓርቲ ዓላማ እና እሴቶች፣ የትኩረት አቅጣጫዎች እንዲሁም የትግራይ ሕዝብ ከብልፅግና ፓርቲ አኳያ አሁን ያለበት ነባራዊ ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዬች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
ዘጋቢ፡- ሀያት መኮነን -ከደሴ እና አዳሙ ሺባባው ከባሕር ዳር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m