በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተገነባው አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡

799

ባሕር ዳር፡ መስከረም 28/2013ዓ.ም (አብመድ) በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት በ29 ሚሊዮን ብር የተገነባው አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል።

በወረዳው ጦሳ ፈላና ቀበሌ የተገነባው አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2011 ዓ.ም ነበር ግንባታው የተጀመረው።

ትምህርት ቤቱ በወረዳው ሁለት ብቻ የነበረው የትምህርት ቤት ቁጥር ከማሳደጉም ባለፈ ከ12 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘው ይማሩ የነበሩ ተማሪዎችን እንግልት እንደሚያስቀር ታውቋል።

በ29 ሚሊዮን ብር የተገነባው ትምህርት ቤቱ 18 የመማሪያ ክፍሎች፣ ሁለት ቤተ ሙከራዎችና ቤተ መጻሕፍት አለው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) እና ሌሎች የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አበሻ አንለይ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበአማራ ክልል 740 ሺህ ሄክታር መሬት በመጤ አረም መወረሩን ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ አስታወቀ፡፡
Next articleከውጭ የሚገባን ስንዴ ከ50 በመቶ በላይ ለመቀነስ እየሠራ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡