ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነውን ጎርጎራን ጎብኝተዋል፡፡

161

ባሕር ዳር፡ መስከረም 27/2013ዓ.ም (አብመድ) ዛሬ ረፋድ የባሕር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክን የመረቁት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነውን ጎርጎራንም ጎብኝተዋል።

በሀገር ደረጃ ሦስት መዳረሻዎችን በ3 ቢሊዮን ብር ለማልማት በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብሮች እየተከናወኑ ነው።

በጎርጎራ ፕሮጀክት የቱሪስት ፍሰትን ለመሳብና የአካባቢውን ጸጋ አልምቶ ለመጠቀም የተለያዩ ልማቶችን ለመተግበር ታቅዷል።
ዘመናዊ ካፌና ሬስቶራንት፣ የብስክሌትና ፈረስ መጋለቢያ፣ ባህላዊ መንደሮች ልማት፣ የግብርና ምርምር፣ የዓሳ ማስገሪያ መዳረሻን ማልማትና ተያያዥ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለበት ወቅት የጎዳና ተዳዳሪዎች መጠለያ ሆነው የቆዩ ትምህርት ቤቶችን የፀረ ተዋስያን ርጭት ማድረግ ጀመረ፡፡
Next articleየበረሃ አንበጣ መንጋን የመከላከል ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ፡፡