የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል መንግሥት ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ተገቢና ትክክለኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት አስታወቀ።

274

ጥምረቱ አገር ወዳዱ የትግራይ ሕዝብ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ተቀብሎ ጎጠኛውን ቡድን ማስወገድ እንዳለበት ጥሪ አቅርቧል።

የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሰብሳቢ ደረጀ በቀለ ዛሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ማብራሪያ እንደተናገሩት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሳለፈው ውሳኔ የትግራይ ክልል ሕዝብን ያከበረ ነው።

ጥምረቱ የተወሰኑ ጎጠኛ ቡድኖች የክልሉን ሕዝብ ስለማይወክሉ የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት የተለላፈው ውሳኔ ተገቢና ትክክል ነው ብሎ ያምናል።

“ጥቂት ጎጠኞች ;በክልላቸን ማንም አያገባውም’ እያሉ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ቆይተዋል” ያሉት አቶ ደረጀ እነዚህ ጥቂት ቡድኖች መላውን የትግራይ ሕዝብ ስለማይወክሉ የፌዴረሽን ምክር ቤት በዚህ አግባብ ውሳኔ ማሳለፉ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ገልፀዋል።

“የተላለፈው ውሳኔ በቂ አይደለም” ያሉት አቶ ደረጀ ማንም እየተነሳ እኔ ነኝ ትክክል ሕዝቡን እኔ ነኝ መምራት ያለብኝ እያለ መፎከሩ ትክክል ስላልሆነና ሕዝቡን የማይወክልም እስከሆነ ድረስ የፌዴራል መንግሥት ያለውን ኃይል አማራጭ ሁሉ ተጠቅሞ እነዚህን ጥቂት ጎጠኞች ማስወገድ አለበት ነው ያሉት።

“መንግሥት ኃይሉን የሚያሰባስበው ወይም የሚጠቀመው ለውጭ ጠላት ብቻ አይደለም” ያሉት አቶ ደረጀ በአገር ውስጥም እንደዚህ ዓይነት ጎጠኞችንና በሕዝብ ላይ ጫና የሚፈጥሩ ቡድኖችን ማስወገድና ሥርዓት ማስያዝ አለበት፤ ይህ የማይሆን ከሆነ ሁሉም እየተነሳ የሰፈር ጀብደኛ መሆኑ አይቀርም” ሲሉ አሳስበዋል።

በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው አገር ወዳዱ የትግራይ ሕዝብ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ተቀብሎ በአንድነት ተነስቶ እነዚህን ጎጠኞች አስወግዶ ከተቀረው ወንድምና እህቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አብሮ እንዲጓዝም ጥሪ አቅርበዋል።

“በጥቂት ጎጠኞች የተነሳ የትግራይ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ልማትና አስተዳደር መነጠል የለበትም” ያሉት አቶ ደረጀ “የእነዚህን ማንአለብኝ የሚሉ ጎጠኞች አካሄድ ተረድቶ ከላዩ ላይ ማስወገድና አደብ ማስገዛት አለበት፤ ይሄንን ማድረግ ካልቻሉ የማታ ማታ ዋናው ተጎጂ የሚሆነው ሕዝቡ ነው” ብለዋል።

የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ከዚህ በፊት ህወኃትን ከጥምረቱ ማባረሩን አስታውሶ ኢ.ፕ.ድ ዘግቧል።

Previous articleየአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አራተኛ የወንጀል ችሎት የሰኔ 15 ጥቃት ምስክሮችን ከሰዓት በኋላ መስማት ይጀምራል፡፡
Next articleበወረባቦ ወረዳ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ መንጋ በ11 ቀበሌዎች ያለ ሰብልን ሙሉ በሙሉ ማውደሙን የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ፡፡