ይናጋ ዘንባባው ይናጋ በባሕርዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ዛሬ ከፍ ብሎ ይደመጣል በጣና ሞገዶቹ ደጋፊዎች።

0
35

የጣና ሞገዶቹ በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም መቻልን ይጋብዛሉ።

ዛሬ በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ ሲካሄድ አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ከዛሬ ጨዋታዎች መካከል የጣና ሞገዶቹ በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም መቻልን የሚያስተናግዱበት ጨዋታ ይጠበቃል።

ሁለቱ ክለቦች እስካሁን 12 ጊዜ ተገናኝተዋል። በግንኙነታቸው አምስቱ ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቅ አራቱን የጣና ሞገዶቹ አሸንፈዋል። ቀሪዎቹን ሦሥት ጨዋታዎች ደግሞ መቻል አሸንፏል።

ሁለቱ ክለቦች 12 ጊዜ መረባቸውን በማስደፈር ተመሳሳይ ያደርጋቸዋል።

የሁለቱን ጨዋታዎች ስንመለከት የግብ ማስቆጠር ችግር እንደሌለ የሚያሳይ ነው።

ዛሬስ ባሕር ዳር ከተማ ወይስ መቻል ማን ያሸንፋል ግምታችሁን ከነምክንያቱ አስቀምጡ? ጨዋታውም 10፡00 ላይ ነው የሚካሄደው። ይናጋ ዘንባባው ይናጋ በባሕርዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ከፍ ብሎ ዛሬ ይደመጣል።

አዳማ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ አዳማ ላይ 9፡00

ቅዱስ ጊዮርጋስ ከወላይታ ዲቻ አዲስ አበባ ላይ 9፡30 ላይ

ነገሌ አርሲ ከ ሲዳማ ቡና አዳማ ላይ 12፡00 ላይ ይጫዎታሉ።
#አሚኮ #ስፖርት

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_20_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here