6ኛው ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በተካሄደ ጨዋታ ባሕርዳር ከተማን ከኢትዮጵያ መድን ያገናኘው ጨዋታ በባሕር ዳር ከተማ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ባሕርዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ 1 በኾነ ውጤት ነው ያሸነፉት።
የባሕር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች በ10ኛው ደቂቃ ዮዳሄ ዳዊት፣ በ39ኛው ደቂቃ አንተነህ ተፈራ እና በ90+4 ደቂቃ ደሳለኝ አሻግሬ አስቆጥረዋል።
የኢትዮጵያ መድንን የማስተዛዘኛ ግብ ደግሞ
በ 68ኛው ደቂቃ ወገኔ ገዛኸኝ አስቆጥሯል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_12_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



