ማንቸስተር ሲቲ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፉልሃምን አስተናግዶ 1 ለ 1 በኾነ ውጤት ተለያይቷል። አንደርሰን በሁለተኛው አጋማሽ ከሳጥን ውጪ ያስቆጠራት ድንቅ ግብ ሲቲ ከአንድ ወር በላይ ቆይታ በኋላ የመጀመሪያውን የፕሪሚየር ሊግ ነጥብ እንዲያገኝ አስችላዋለች።
በጨዋታው ፉልሃሞች በመጀመሪያ ሙከራቸው ቦብ የሲቲን ተከላካዮች አልፎ ያቀበለውን ኳስ ሮድሪጎ ሙኒዝ ወደ ግብነት በመቀየር መሪ መኾን ችለው ነበር።
በጨዋታው የማንቸስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ዶናሩማ የቦብ፣ የሮድሪጎ ሙኒዝ እና የባሲ ዒላማ የጠበቁ ሙከራዎችን አድኗል። ይህ ውጤት ማንቸስተር ሲቲ በሁሉም ውድድሮች በፉልሃም ላይ የነበረውን 20 ተከታታይ የማሸነፍ የእንግሊዝ ክብረ ወሰን የገታ ሲኾን ከፈረንጆቹ 2011 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፉልሃምን ማሸነፍ አልቻለም።
በኤንዞ ማሬስካ የሚመራው ማንቸስተር ሲቲ ያለፉትን ሦሥት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ተሸንፎ የነበረ ሲኾን በዚህኛው ጨዋታ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል። በአልቫሮ አርቤሎአ የሚሰለጥነው ፉልሃም በበኩሉ በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞውን ማስቀጠል ችሏል።
ጨዋታውን ተከትሎ ሲቲ በ22 ነጥብ በብራይተን በግብ ክፍያ ተበልጦ ሦሥተኛ ሲቀመጥ አርሰናል በ27 ነጥብ አንድ ጨዋታ እየቀረው ሊጉን ይመራል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_12_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



