ማንቸስተር ዩናይትድ ለአሠልጣኞች ቅጥር እና ስንብት ያወጣው ወጪ ወደ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ተጠጋ።

0
39

ማንቸስተር ዩናይትድ አርጀንቲናዊውን ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን አዲሱ ዋና አሠልጣኝ አድርጎ ከሾመ ከሦሥት ቀናት በኋላ ተጨማሪ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ብድር መውሰዱን አስታውቋል። ክለቡ ይፋ ባደረገው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የፋይናንስ ሪፖርት መሠረት፣ ፖቼቲኖን ከአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ለማስለቀቅ 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ፓውንድ ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል።

ይህንን ተከትሎ ክለቡ ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን መልቀቅ 2013 ወዲህ አሠልጣኞችን ለመቅጠር እና ለማሰናበት ያወጣው ጠቅላላ ወጪ 95 ሚሊዮን ፓውንድ ደርሷል። ለፖቼቲኖ ቅጥር እና በቅርቡ ለተሰናበቱት ማይክል ካሪክ የሚከፈለው ካሳ ሲታከልበትም ወጪው ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚበልጥ ተገምቷል።

ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ እጅግ መጥፎ የሚባል የውድድር ዘመን አጀማመር አድርጎ ወራጅ ቀጣና ውስጥ የሚገኘው ዩናይትድ፣ ባለፈው ሳምንት ማይክል ካሪክን ከኀላፊነት ማሰናበቱ ይታወሳል። ፖቼቲኖ ከፈርጉሰን በኋላ ክለቡን የተረከቡ ዘጠነኛው ቋሚ አሠልጣኝ ሲኾኑ ክለቡ ባለፉት ሦሥት ተከታታይ የውድድር ዘመናት በውድድር አጋማሽ ላይ አሠልጣኝ ለመቀየር ተገዷል።

በተጨማሪም የክለቡ የፋይናንስ መግለጫ እንደሚያሳየው፣ ዩናይትድ የወሰደውን አዲስ ብድር ጨምሮ አጠቃላይ የብድር ዕዳው 240 ሚሊዮን ፓውንድ የደረሰ ሲኾን፣ ለተጫዋቾች ዝውውር ያልተከፈለ 417 ሚሊዮን ፓውንድ ዕዳ እንዳለበትም ታውቋል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_12_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here