የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ውድድር የሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ድልድል ይፋ ኾኗል።
በኔሽንስ ሊጉ ሩብ ፍፃሜ የደረሱት በሊግ ኤ ውስጥ በአራት ምድቦች በተካሄዱ ጨዋታዎች ከየምድቡ 1ኛ እና 2ኛ ኾነው ያጠናቀቁ 8 ሀገራት ናቸው።
ለእነዚሁ ሀገራት የሩብ ፍፃሜ የጨዋታ ድልድል ዛሬ ይፋ ሲደረግ ስፔን ከፈረንሳይ የተገናኙበት መርሐ ግብር ከወዲሁ ተጠባቂ ኾኗል።
በሌሎች 3 የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ደግሞ ኖርዌይ ከእንግሊዝ፣ ኔዘርላንድስ ከፖርቹጋል እና ቤልጅየም ከጀርመን ተገናኝተዋል።
የግማሽ ፍፃሜ ድልድሉም አንድ ላይ ይፋ የተደረገ ሲኾን በዚህም የስፔን እና ፈረንሳይ አሸናፊ ከኔዘርላንድስ እና ፖርቹጋል አሸናፊ፤ የኖርዌይ እና እንግሊዝ አሸናፊ ደግሞ ከቤልጂየም እና ጀርመን አሸናፊ ጋር እንደሚገናኙ ቢቢሲ ዘግቧል።
በኃይሌ አበራ
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_11_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



