ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በተለያዩ ሀገራት በተካሄደ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡ በቻይና ሁዋን ከተማ በተካሄደ የሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት ማሬ ዲባባ ርቀቱን 2 ሰዓት 25 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ በማጠናቀቅ ቀዳሚ ኾናለች፡፡
በተመሳሳይ በጣልያን ሚላኖ ከተማ በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት አንቺናሉ ደሴ 1 ሰዓት 07 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ በኾነ ሰዓት በመግባት አሸንፋለች፡፡ በቻይና ቼንግዱ በተካሄደ የወንዶች ማራቶን ውድድር አትሌት ፈቃዱ መርጋ ርቀቱን በ2 ሰዓት 16 ደቂቃ ከ9 ሰከንድ በማጠናቀቅ ሲያሸንፍ አትሌት በለጠ መኮንን ደግሞ 2ኛ ደረጃን ይዟል፡፡
በሌላ በኩል በቻይና ውዢ ከተማ በተካሄደ የማራቶን ውድድር ታዱ አባተ ርቀቱን 2 ሰዓት 6 ደቃቃ ከ18 ሰከንድ በኾነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸንፏል፡፡ በዚሁ ርቅት አትሌት አባይ አለሙ ውድድሩን 2 ሰዓት 6 ደቀቂ ከ50 ሰከንድ በማጠናቀቅ ሁለተኛ ደረጃን መያዝ ችሏል፡፡ በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በተካሄደ የ8 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድርም በሪሁን ፈዬ 1ኛ፣ ገመቹ ቶለሳ 2ኛ እና አየንሳ አለሙ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቃቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!