የ2019 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 20 ክለቦችን በ1 ምደብ እንደሚያፎካክር ቀደም ብለን መጥቀሳችን ይታወሳል፡፡ በመድረኩ አማራ ክልልን ከሚወክሉት መካከል የሆነው ደሴ ከተማ የ2019 የኢትዮጰያ ከፍተኛ ሊግ ውድድሩን ከምድረ ገነት ሽረ ጋር በማድረግ ይጀምራል፡፡
ድልድሉ ይፋ ሲሆን ደሴ ከተማ ድሬደዋ ላይ ደብረ ብርሃን ከተማ ደግሞ ሀዋሳ ከተማ ላይ ጨዋታቸውን ይደርጋሉ፡፡ በድሬደዋ ከተማ ምድብ ባቱ ከተማ፣ ቢሾፍቱ ከተማ፣መልካ ኖኖ፣ ሆሞሻ ሸንጋ፣የካ ክ/ከተማ፣ሱሉልታ ክ/ተማ፣ምድረገነት ሽረ፣ ደሴ ከተማ፣ ልደታ ክ/ከተማ ና ሻሸመኔ ከተማ ይገኙበታል፡፡
ሀዋሳ ከተማ ላይ በሚደረገው ምድብ ደግሞ ይርጋጨፌ ቡና ፣ ቡራዩ ክ/ከተማ፣አዲስ ከተማ ፣አርባ ምንጭ ከተማ፣ደብረ ብርሃን ከተማ ፣ቤንች ማጂ ቡና፣መቐለ 70 እንደርታ፣ መንጌ ቤላሻንጉል፣ ድሬዳዋ ከተማ ና ንብ ተደልድለዋል፡፡
ህዳር 5 የ2019 ከፍተኛ ሊግ ውድድር ይጀመራል፡፡
ሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



