የሮናልዶ የስንብት መልዕክት!

0
69
ደሴ፣ ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም (አሚኮ ደሴ) የ41 ዓመቱ አጥቂ ክርስትያኖ ሮናልዶ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ከዘለቀ ግልጋሎት በኋላ ከሀገሩ ፖርቹጋል ጋር የነበረው ጉዞ መቋጨቱን ይፋ አድርጓል።
ክርስትያኖ ለመጨረሻ ጊዜ ለብሔራዊ ቡድኑ ተሰልፎ የተጫወተው ከዌልስ ጋር በተደረገ ጨዋታ ሲሆን በሚቀጥለው ጨዋታ ላይ ተጠባባቂ ሆኖ ሳይሰለፍ በመቅረቱ ምክንያት የፖርቹጋልን ልምምድ ካምፕ ለቆ መውጣቱ ይታወሳል።
ሮናልዶ በዚህ ድርጊቱም የ255 ዩሮ የገንዘብ መቀጮ እና የ30 ቀናት እገዳ ተጥሎበት ነበር። በወቅቱ ውሳኔውን በሚያስረዳው እና ለቡድን አጋሮቹ ይቅርታ በጠየቀበት ባለ 1,740 ቃላት መግለጫው ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን እንደማያገል ተናግሮ ነበር።
ሆኖም በዛሬው ዕለት ክርስትያኖ ሮናልዶ በማህበራዊ ትስስር ገፆቹ ባወጣው መግለጫ ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።
ሮናልዶ በመግለጫው “የብሔራዊ ቡድናችንን ቁጥር 7 ማሊያ መልሼ የማስረክብበት ቀን ደርሷል። ማሊያው ለእኔ ብቻ የተሰጠ እንደሆነ ተሰምቶኝ አያውቅም። ነገር ግን ለ23 ዓመታት ያህል በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ስታዲየሞች ውስጥ ለብሼዋለሁ፣ ተከላክዬለታለሁ፣ እንዲሁም
በታላቅ ኃላፊነት እና ክብር ይዤው ተጉዣለሁ። ዛሬ ግን ይህንን ማሊያ ለወደፊቱ ትውልድ የማስተላልፍበት ጊዜ ደርሷል ቀላል ውሳኔ አልነበረም” ሲል ተደምጧል።
ሮናልዶ “በነሃሴ 2003 ተጀምሮ ሕይወቴን ለዘለዓለም የለወጠው ጉዞ አሁን ፍጻሜ አግኝቷል። ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ያሳለፍኩትን ሁሉ ወደኋላ ተመልሼ ስመለከት፣ ጨዋታዎችን፣ ግቦችን፣ ክብረ ወሰኖችን ወይም ዋንጫዎችን ብቻ አይደለም የማየው። ግቦች ይረሳሉ። ዋንጫዎች
በቤተ-መዘክሮች ውስጥ ይቀመጣሉ። ክብረ ወሰኖችም በጊዜ ሂደት ይሰበራሉ። ነገር ግን ጊዜ ሊያጠፋው የማይችለው አንድ ነገር አለ በሰዎች ልብ ውስጥ የምንይዘው ስፍራ ነው” ብሏል።
በእግር ኳስ ታሪክ እንደ ክርስትያኖ ሮናልዶ ብዙ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ያደረገ እንዲሁም ብዙ ግቦችን ያስቆጠረ ተጨዋች የለም እርሱም በብዙዎች ዘንድ ከዓለም የምንግዜም ታላላቅ እግር ኳስ ተጫዋቾች አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል።
የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው በፈረንጆቹ 2003 የመጀመሪያ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን ያደረገ ሲሆን ከፖርቹጋል ጋር የ 2016ቱን የአውሮፓ ዋንጫ እና
ሁለት የኔሽንስ ሊግ ዋንጫዎችን አሸንፏል።
ሮናልዶ በክረምቱ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ፖርቹጋል በ16ቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከመሰናበቷ በፊት ሶስት ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን ከውድድሩ በፊትም የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የመጨረሻው እንደሚሆን ተናግሮ ነበር።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
“ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርስዎ የፌስቡክ ገጻችንን ‘Follow’ ያድርጉ።
ሊንኩን ተጭነው ቤተሰብ ይሁኑ፦ 👇
“መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ – ስለመረጡን እናመሰግናለን!”
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here