ከፍተኛ ሊጉ በአዲስ የውድድር ቅርፅ ይጀመራል።

0
28
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የሚያዘጋጀው የከፍተኛ ሊግ የ2019 የውድድር ዘመን የዕጣ ማውጣት መርሀግብር ተካሂዷል።
ያለፉትን አመታት በሁለት ምድቦች እየተከፈለ ይደረግ የነበረ ሲሆን በዘንድሮው የውድድር ዘመን በ20 ቡድኖች መካከል በአንድ ምድብ ብቻ እንዲደረግ ተወስኗል።
ይህ ሲሆን በውድድሩ የነጥብ ብልጫ ያስመዘገቡ አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው የሚያጠናቅቁ ክለቦች ወደ 2020 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያድጋሉ።
አምስት ክለቦች ደግሞ ወደ አንደኛ ሊጉ እንደሚወርዱ ይፋ ተደርጓል። አማራ ክልል በደሴ ከተማ እና ደብረብርሀን ከተማ ሲወከል፤ ደሴ ከተማ ያለፈው የውድድር አመት በመጨረሻ ጨዋታዎች በጣላቸው ነጥቦች ወደ ፕሪሚየር ሊግ ሳያድግ መቅረቱ ይታዎሳል።
ዘንድሮ የተሻለ ሆኖ ለመቅረብ ቀደም ብሎ በአዲስ አሰልጣኝ እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ አምጥቶ ተዘጋጅቷል።
ውድድሩ ህዳር 5 ጀምሮ በድሬዳዋ እና ሀዋሳ ከተማ ይደረጋል።
ዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here