የሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራዮላ ቡድናችን በተለይም በተጋጣሚ የግብ ክልል ውስጥ የሚፈጥራቸውን ዕድሎች ወደ ግብ በመቀየር ረገድ መሻሻል አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
ሊቨርፑል ዛሬ ምሽት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ከቱርኩ ፌነርባቼ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ በውድድሩ ያለውን የድል ጉዞ ለማስቀጠል ወደ ሜዳ ይገባል።
ቀያዮቹ በውድድር ዘመኑ እስከ አሁን ባደረጓቸው ሦስት ጨዋታዎች ሦስቱንም ያሸነፉ ሲሆን 12 ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል።
የኢራዮላ ልጆች በኘሪሚየር ሊጉ ያላቸው ግብ የማስቆጠር ንፃሬ ግን ከቻምፒዮንስ ሊጉ አኳያ ተቃራኒ ነው።
ሊቨርፑል በዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ማስቆጠር የቻለው 11 ግቦች ብቻ ሲሆን ይባስ ብሎም እሁድ ከአርሰናል ጋር ባደረገው ጨዋታ አንድም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ አላደረገም።
አሰልጣኙ ቡድናቸው በአርሰናል ላይ ያሳየውን አጠቃላይ አቋም ቢያደንቁም በተጋጣሚ የግብ ክልል ውስጥ ያለው የተጫዋቾቻቸው እንቅስቃሴ እና የግብ ዕድሎችን በአግባቡ የመጠቀም ክፍተት እንዳሳሰባቸው ጠቁመዋል።
ዛሬ ምሽት ከፌነርባቼ ጋር በሚደረገው ጨዋታ አሰልጣኙ ችግራቸውን በመቅረፍ የቻምፒየንስ ሊግ የድል ጉዟቸውን ለማስቀጠል ወደ ሜዳ ይገባሉ።
ይሁን እንጂ በሜዳው የሚጫወተው ፌነርባቼ በደጋፊዎቹ ታግዞ ጨዋታውን ከባድ እንደሚያደርግባቸው ይጠበቃል።
ሀሚድ አብደላ (የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምሕርት የተግባር ተለማማጅ)
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



