”ምንም አይነት እፎይታ አልተሰማኝም”ካሪክ

0
48
የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ የሆኑት ማይክል ካሪክ ከምሽቱ ወሳኝ የቻምፒየንስ ሊግ ድል በኃላ በሰጡት አስተያየት ምንም አይነት እፎይታ አልተሰማኝም በማለት ተናግረዋል ።
በኦልድ ትራፎርድ ከጣሊያኑ ክለብ ሮማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 ከመመራት ተነስተው 3ለ2 ማሸነፍ የቻሉት ቀያይ ሰይጣኖቹ ባለፉት 9 ጨዋታዎች ገጥሟቸው የነበረውን ያለ ማሸነፍ ጉዞ መስበር የቻሉበት ጨዋታ ሆኖ አልፏል ።
ከጨዋታው በኋላ ሀሳባቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ደጋፊዎች እና ተጨዋቾች የተመኙትን ድል ስላገኙ እንደተደሰቱ በመግለፅ ነገር ግን ከመጠን በላይ መደሰት እንደሌለባቸው እና ትኩረታችንን ወደ ቀጣይ ጨዋታዎች ማድረግ አለብን በማለት ተናግረዋል።
በአሁኑ የፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ 17ተኛ ላይ የሚገኙት ቀያይ ሰይጠኖቹ በቀጣይ ከአስቶንቪላ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል ።
‎ኤርምያስ ገረመው (የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምሕርት የተግባር ተለማማጅ)
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here