ሮሚዮ ላቪያ ከአሰልጣኝ ዣቪ አሎንሶ አድናቆት ደርሶታል።

0
48
 ተጫዋቹ በ4 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ 2 ሙሉ ጨዋታ አከናውኗል። ቤልጅየማዊው አማካኝ በ2023 ከሳውዛምፕተን ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ከመጣ በኋላ በጉዳት በእጅጉ ተፈትኗል።
የ22 ዓመቱ ተጫዋች ከ4 ዓመታት በኋላ በ72 ሰዓታት ውስጥ ከሊቨርፑል እና ማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ሙሉ 90 ደቂቃ ተጫውቷል።
በተለይ በፕሪሚየር ሊጉ ቼልሲ ማንቸስተር ዩናይትድን 2ለ0 በረታበት ጨዋታ ያሳየው ብቃት ከአሎንሶ አድናቆት እንዲደርሰው አድርጓል።
የአማካኝን ሚና ከማንም በላይ የሚረዳው አሰልጣኝ አሎንሶ ሮሚዮ ላቪያ በመጨረሻም በስታምፎርድ ብሪጅ አዲስ ምዕራፍ መክፈቱን በማወደስ ተናግሯል።
“‎ላቪያ በማንችስተር ዮናይትድ ጨዋታ ትክክለኛ ውሳኔ በመወሰን፣ በአልበገርባይነት እና ተከላካዮችን ከአጥቂዎች በማገናኘት ድንቅ ብቃት” አሳይቷል ያለው አሎንሶ ተጫዋቹ በራስ መተማመኑ ስለመመለሱ አረጋግጠዋል።
ቃልኪዳን ምስክር (የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምሕርት የተግባር ተለማማጅ)
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here