የኢትዮጵያ የሴቶች እጅ ኳስ ብሔራዊ ቡድን ለዞን 5 ውድድር ወደ ታንዛኒያ አቀና።

0
50
የኢትዮጵያ የሴቶች እጅ ኳስ ብሔራዊ ቡድን ልዑካን በዞን 5 የዓለም አቀፍ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን (IHF) ውድድር ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ማለዳ ወደ ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም አቅንቷል።
በዚህ የቀጠናው የምስራቅ አፍሪካ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ቡሩንዲ፣ ኡጋንዳ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማልያ ብሄራዊ እጅ ኳስ ቡድኖች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለዚህ ውድድር ዝግጅት ሲያደርግ የነበረው ብሔራዊ ቡድኑ ከአዲስ አበባ ከተማ 7 እንዲሁም ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከዱራሜ እና ከሀድያ 9 ተጫዋቾችን አካቷል።
ልኡካን ቡድኑ በጠቅላላው 19 አባላትን ይዞ ወደ ስፍራው አቅንቷል።
ሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here