የአስፈሪውን የባርሴሎና ግስጋሴ የሚያስቆም እስካሁን አልተገኘም።

0
144
በስፔን ላሊጋ 9ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባርሴሎና ከሜዳው ውጪ ሪያል ቤትስን ገጥሞ የዓለማችን ምርጡ ቡድን መኾኑን ያረጋገጠበትን ድል አስመዝግቧል።
5 ለ 2 በኾነ ሰፊ ውጤት ሪያል ቤትስን ያሸነፈው ባርሴሎና ማን ከግስጋሴው ሊያስቆመው ይችላል የሚመለው ሃሳብ በስፖርት ቤተሰቡ እንዲነሳ አድርጓል።
በጨዋታው ባርሴሎናን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ በ10ኛው ደቂቃ ላይ ላሚን ያማል ከመረብ አሳርፎ ባርሴሎና መሪ ሆኗል።
ሪያል ቤትሶች በ27ኛው ደቂቃ በጎሜዝ አማካኝነት መረቡን የደፈሩበት እና አቻ መኾን የቻሉበትን ግብ ማስቆጠር ችለው ነበር።
ጨዋታውን በደንብ ያነበቡት ባርሴሎናዎች በ41ኛው ደቂቃ በሮድሪ አማካኝነት ሁለተኛ ግብ አስቆጥረው እንደገና መሪ መኾን ቻሉ።
ከዛም በ51ኛው ደቂቃ ጋብሬል ጄሱስ የባርሴሎናን መሪነት ወደ 3 ለ 1 ያሳደገበትን እና የቡድኑን አስፈሪነት ያረጋገጠበትን ግብ አስቆጥሯል።
ሪያል ቤቲስ በ54ኛው ደቂቃ በኤዛልዙሊ ግብ ልዩነቱን ወደ አንድ ዝቅ ቢያደርጉም እንደንብ ገንፍለው የተነሱት ባርሴሎናዎች በ62ኛው ደቂቃ በኤሪክ ጋርሲያ እንዲሁም በ81ኛው ደቂቃ በዳኒ ኦልሞ አማካኝነት ዓለም ላይ ያለ ምርጥ ጥምረት መኾኑን ያሳዩበትን ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ለዓለም ያሉበትን ደረጃ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዚህም ባርሴሎና በ27 ነጥብ መሪነቱን ያጠናከረ ሲኾን ሪያል ቤቲሶች በ19 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ይህን ግስጋሴ ታዲያ በቀጣይ ሳምንት ኤል ክላሲኮ የሚያገኘው ሪያል ማድሪድ ያስቆመው ይኾን ወይስ እሱም እንደሌሎቹ ክለቦች ሦሥት ነጥቡን አሳልፎ ይሰጣል የሚለው ይጠበቃል።
በሌላ ጨዋታ አትሌቲኮ ስፓኞልን 1ለ0 አሸንፎ ነጥቡን 22 በማድረስ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።
ኢልቸ እና ቪያሪያል ደግሞ ያለምንም ግብ ነጥብ ተጋርተዋል።
ሪያል ማድሪድ ደግሞ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ18 ነጥብ ወአራተኛ ደረጃ ተቀምጧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here