ፊፉ ዋና ስራ አስፈፃሚውን ኬቭን ላሞር አሰናበተ።

0
10
ላሞር የፊፋ ፕሬዝዳንት ጅያኒ ኢንፋንቲኖን የተቋሙን የውድድር ድርሻ ለግል ባለሀብት የማስተላለፍ ሀሳብ በወቃወሙ ነው ተብሏል።
ለሁለት አመት የፊፋ የውስጥ ተቋማዊና እና የውጭ ስራዎች ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ያገለገሉትን ኬቭን ላሞር ‘ለነበረህ ጊዜ እናመሠግናለን ።
የስራ ትስስራችን ግን አብቅቷል’ በሚል ትናንት አሰናብቶታል።
የስንብት ትዕዛዙ ከፊፋ ፕሬዝዳንት ጅያኒ ኢንፋንቲኖ የወረደ እንደሆነ የገለፀው ቢቢሲ ኬቭን ላሞር ፊፋ የተቋሙን ድርሻ ለግል የመሸጥ እቅድ የአንድ ግለሰብ ወይም የኢንፋንቲኖ ብቻ መሆኑን ቀደም ብሎ ማጋለጡ ለዚህ ምክንያት እንደሆነ አስረድቷል።
መለሰ ግዛቸው
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here