የ2025/26 የውድድር ዘመን የፕሪሚየር ሊግ አክሊልን ከ22 ዓመታት ጥበቃ በኋላ የደፉት መድፈኞቹ፣ የውድድር ዓመቱን በኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫ ጀምረዋል።
ባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠው አርሰናል፣ ዘንድሮም ክብሩን ለማስቀጠልና አዳዲስ ፈተናዎችን ለመጋፈጥ ተዘጋጅቷል።
የሚካኤል አርቴታ ሰራዊት ዙፋኑን ማስጠበቅ ከማሸነፍ በላይ ከባድ መሆኑን ቢረዳም ፣ የክለቡን ወርቃማ ጊዜ ለማስቀጠል የውድድር ዓመቱን በትልቅ ስነ-ልቦናዊ ልዕልና ይጀምራል።
ማንቸስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ሌሎች የሊጉ አንጋፋ ክለቦች ለታላቁ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ፍልሚያ ራሳቸውን አዘጋጅተዋል።
ሆኖም በሰሜን ለንደን ሰማይ ስር ያለው መንፈስ ግን የተለየ ነው። አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በልምድ ማዕከሉ ለተጫዋቾቹ ያስተላለፉት መልእክት ግልጽ ነው፦
”ዋንጫ ማንሳት አንዱና ትልቁ ስኬት ነው፤ ነገር ግን ያንን ዙፋን አስጠብቆ መቆየት የምርጦች ምርጥ መለያ ነው።”
መድፈኞቹ አዲሱን የውድድር ዘመን ፈተናዎች ለመጋፈጥ፣ የድላቸውን ታሪክ በድጋሚ ለመጻፍ እና የሰሜን ለንደንን ክብር ከፍ አድርገው ለመስቀል የፕሪሚየር ሊጉን መጀመር ይጠብቃሉ።
ታደሰ ሙላት
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



