አርን ስሎት የክለብ ሥራ ምርጫቸው መኾኑን ተናገሩ።

0
38
የቀድሞው የሊቨርፑል አሠልጣኝ አርን ስሎት የኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቡድን ሥራን ውድቅ አድርገዋል።
“በየቀኑ ተጫዋቾችን ማግኘት እና ማሠልጠን እፈልጋለሁ፤ የብሔራዊ ቡድን ሥራ ደግሞ ይህን ዕድል አይሰጠኝም” ብለዋል የ47 ዓመቱ ስሎት።
በደመወዝ እና በውል ጉዳይ ከኔዘርላንድስ ጋር ምንም አይነት ንግግር አላደረግንም ያሉት ስሎት በዚህ ዕድሜዬ የክለብ ሥራ ምርጫዬ ነው ብለዋል።
የኔዘርላንድስ እግር ኳስ ማኅበር ሮናልድ ኮመንን ለመተካት ራይዚገርን እና ሮቤርቶ ማርቲኔዝን በእጩነት መያዙን ያሆ ስፖርት አስነብቧል።
ዘጋቢ፦ ንዋይ ሙሉጌታ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here