ሶማሊያዊው ዳኛ ዑመር አርታን በአውሮፓ ሱፐር ካፕ ታሪክ ሊሠሩ ነው።

0
127
ሶማሊያዊው የመሐል ዳኛ ዑመር አርታን ፓሪስ ሴንት ዠርሜን ከአስቶን ቪላ የሚያደርጉትን የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫ ጨዋታን በመምራት የመጀመሪያው አውሮፓዊ ያልኾኑ ዳኛ በመኾን አዲስ ታሪክ ሊጽፉ ነው።
ዳኛው ቀደም ሲል ለ2026 የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ለመዳኘት ወደ አሜሪካ ለመግባት ያቀረቡት የመግቢያ ፈቃድ ቪዛ ውድቅ ተደርጎባቸው የነበረ ቢኾንም አሁን ግን በዓለም አቀፍ ዳኝነት ሥራቸው ትልቅ የተባለ ታሪካዊ ዕድል ገጥሟቸዋል።
እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ ነሀሴ 6/2018 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ታላቅ መርሐ ግብር ዑመር አርታን ጨዋታውን በመምራት በአውሮፓ ሱፐር ካፕ ታሪክ የመጀመሪያው አፍሪካዊ እና አውሮፓዊ ያልኾኑ ዳኛ በመኾን ስማቸውን በታሪክ ያሰፍራሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here