የ2027ቱ የስፔን ሱፐር ካፕ በቱርክ ሊካሄድ እንደሚችል ተገለጸ።

0
66
የ2027 የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር ከሳውዲ አረቢያ ውጭ በቱርኳ ታሪካዊ ከተማ ኢስታንቡል ሊካሄድ እንደሚችል ታዋቂው የስፔን ስፖርት ጋዜጠኛ አልፍሬዶ ማርቲኔዝ ዘግቧል።
እንደዘገባው ጨዋታው በፈረንጆቹ የካቲት 2027 መጀመሪያ ላይ በቱርክ ኢስታንቡል እንዲካሄድ ታቅዷል።
በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታም ሪያል ማድሪድ ከ ሪያል ሶሲዳድ እንዲሁም ባርሴሎና ከ አትሌቲኮ ማድሪድ ይጫወታሉ።
ሁለቱ የስፔን ገናና ክለቦች ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ የግማሽ ፍፃሜ ተፎካካሪዎቻቸውን ካሸነፉ በኢስታንቡል በሚካሄደው የዋንጫ ጨዋታ ‘ኤል ክላሲኮ’ን ያካሂዳሉ።
በውድድሩ አስተናጋጅነት ዙሪያ ከስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኩል እስካሁን ይፋዊ ማረጋገጫ ያልተሰጠ ቢኾንም ኢስታንቡል ውድድሩን የማስተናገድ ከፍተኛ እድል ካላቸው ከተሞች አንዷ እንደኾች ቱርክ ቱደይ የተሰኘ ድረገጽ አስነብቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here