የአርሰናል ባለሀብቶች በቪኒሽየስ ዝውውር ጉዳይ በድንገት እጃቸውን አስገቡ።

0
265
ሪያል ማድሪድ የብራዚላዊውን ኮከብ ውል ለማራዘም ቢጥርም በደሞዝ ጉዳይ እስካሁን ድረስ አልተስማሙም።
ቪኒሽየስ ውሉን የማያድስ ከኾነ ከአንድ ዓመት በኋላ ማድሪድ ድምቡሎ ሳያገኝ ተጫዋቹን ያጣዋል።
ይህንን ክፍተት ተጠቅመው አርሰናሎች ተጫዋቹን ወደ ለንደን ለማስኮብለል እየሠሩ ነው።
ያሆ ስፖርት እንደዘገበው የአርሰናል ባለቤቶች የክሮንኬ ቤተሰቦች ከቪኒሽየስ ወኪል”ሮክ ኔሽንስ” ጋር ተወያይተዋል።
ባለሀብቶቹ ክለቡን በሱ ዙሪያ ለመገንባት ስለያዙት ኘሮጀክት እና በሳምንት እስከ 400ሺህ ፖውንድ ደሞዝ ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ለወኪሉ አብራርተዋል።
ያም ኾኖ የቪኒሽየስ ጁኒየር ተቀዳሚ ምርጫው የማድሪዱ ክለብ መኾኑን ዘገባው አመላክቷል።
በንዋይ ሙሉጌታ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here