ከሰሞኑ በወዳጅነት ጨዋታ የአርጀንቲና ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ኢኳዶርን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በጨዋታው አንድ ኪኪ ራሞስ የተባለ ጥቁር ተጫዋች አርጀንቲናን ወክሎ ተጫውቷል።
ጥቁሮችን በሚያገለው የአርጀንቲና ቡድን ከ44 ዓመታት በኋላ ጥቁር ተጫዋች መታየቱ እንግዳ በመኾኑ መነጋገሪያ ኾኗል።
ነገሩ እንዲህ ነው_ በ2010 በሀይቲ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የመሬት መንቀጥቀጥ አይዘነጋም፤ ከዚህ አስከፊ አደጋ አንድ የ8 ወር ሕጻን በተአምር በሕይወት ተገኝቷል።
ወላጆቹን በአደጋው የተነጠቀው ይህ ሕጻን በማደጎ የማደግ ዓለም የሰጠችው እጣ ፋንታ ኾኗል።
የእግር ኳስ ተሰጥኦን ይዞ የተወለደው ይህ ሕጻን ዕድል እና አጋጣሚ ሰምሮለት አሳዳጊዎቹ ከእግር ኳሷ ምድር የበቀሉ አርጀንቲናውያን ናቸው።
ይህ ጥቁር ሕጻን ዛሬ ላይ አድጎ እና በክህሎት ጎልብቶ ነው እንግዲህ የአርጀንቲናን መለያ ለመልበስ የበቃው።
ጥቁሮችን በአርጀንቲና መለያ ያልለመደው እግር ኳስ አፍቃሪ እና ሚዲያ ጉዳዩን መነጋገሪያ አድርጎታል።
ታዳጊው ኪኪ ራሞስ በክህሎቱ አሳምኖ በአንድ ክፍለ ዘመን “ላ አልቢሰለስቴዎች”ን የወከለ 4ኛው ጥቁር ተጫዋች ኾኗል።
ከ1978 የዓለም ዋንጫ በኋላ ለጥቁሮች ባይተዋር የኾነው የአርጀንቲና እግር ኳስም ነገሩ ከዘረኝነት ትችት ማምለጫ መንገድ ኾኖለታል።
በንዋይ ሙሉጌታ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



