የ2026 ዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች በቁጥር ሲለኩ።

0
74

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ለመጀመሪያ ጊዜ 48 ሀገራት የተሳተፉበት ታሪካዊው የ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ምሽት ተጠናቀዋል። በሜዳ ላይ ከተመዘገቡ ድሎች እስከ ስታዲየም ድምቀት ድረስ የተመዘገቡ ዋና ዋና ቁጥራዊ መረጃዎች የሚከተሉትን ይመስላሉ።

በውድድሩ 72 ጨዋታዎች ተደርገዋል።

በግብ ደረጃ 215 ግቦች በአማካይ በየጨዋታው 2 ነጥብ 98 ግቦች ተቆጥረዋል።

4 ሚሊዮን 644 ሺህ ተመልካቾች በሜዳ ተገኝተው ጨዋታዎቹን የመታደም ዕድል አግኝተዋል።

እንደ ኤስ ኤን ፒ መረጃ ከኾነ በምድብ ጨዋታው ሊዮኔል ሜሲ ከአርጀንቲና በ6 ግቦች በከፍተኛ ግብ አግቢነት መሪነቱን ሲይዝ

ኸርሊንግ ሃላንድ ከኖርዌይ 4 ግቦች፣ ኬሊያን ምባፔ ከፈረንሳይ 4 ግቦች፣ ኡስማን ዴምቤሌ ከፈረንሳይ 4 ግቦች፣ ቪኒሺየስ ጁኒየር ከብራዚል 4 ግቦች በማስቆጠር እኩል ኾነው ይከተላሉ።

በተጨማሪም 10 ተጫዋቾች 3 ግቦችን እንዲሁም 23 ተጫዋቾች 2 ግቦችን በምድብ ጨዋታው በስማቸው አስመዝግበዋል።

በምድብ ጨዋታዎቹ ወቅት የታዩ ያልተጠበቁ ክስተቶች እና የቀይ ካርድ ብዛት ስንመለከት 12 ተጫዋቾች በስህተት በራሳቸው መረብ ላይ ግብ አስቆጥረዋል።

በሁሉም የምድብ ጨዋታዎች 10 ተጫዋቾች በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል።

የአፍሪካውያን ተሳትፎ ስናይ በምድብ ጨዋታው አፍሪካውያን አዲስ ታሪክ የጻፉበት ኾኗል።

ወደ ቀጣዩ የጥሎ ማለፍ ደረጃ ካለፉት 32 ሀገራት መካከል ዘጠኙ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው። ይህም አህጉሪቱ በዓለም ዋንጫ መድረክ ላይ ያሳየችውን ከፍተኛ መሻሻል እና ጥንካሬ የሚያሳይ ታሪካዊ ስኬት ኾኖ ተመዝግቧል።

ዛሬም የጥሎ ማለፍ ጨዋታው ሲጀመር

ደቡብ አፍራካ ከ ካናዳ ምሽት 4፡ 00 ላይ ይገናኛሉ።

እርሰዋ ከሁለቱ ክለቦች ማን አሸንፎ ቀጣዩን ዙር ይቀላቀላል ብለው ያስባሉ ሀሳብዎን ያጋሩን።

የጥሎ ማለፉን ድልድል ለመመልከት ያክል፦

🇩🇪 ጀርመን ከ ፓራጓይ 🇵🇾
🇫🇷 ፈረንሳይ ከ ስዊድን 🇸🇪
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ ከ ካናዳ 🇨🇦
🇳🇱 ኔዘርላንድስ ከ ሞሮኮ 🇲🇦
🇵🇹 ፖርቹጋል ከ ክሮሽያ 🇭🇷
🇪🇸 ስፔን ከ ኦስትሪያ 🇦🇹
🇺🇸 አሜሪካ ከ ቦስኒያ 🇧🇦
🇧🇪 ቤልጅየም ከ ሴኔጋል 🇸🇳
🇧🇷 ብራዚል ከ ጃፓን 🇯🇵
🇨🇮 ኮትዲቮር ከ ኖርዌይ 🇳🇴
🇲🇽 ሜክሲኮ ከ ኢኳዶር 🇪🇨
🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿እንግሊዝ ከ ኮንጎ 🇨🇩
🇦🇷 አርጀንቲና ከ ካቦ ቨርዲ 🇨🇻
🇦🇺 አውስትራሊያ ከ ግብጽ 🇪🇬
🇨🇭 ስዊዘርላንድ ከ አልጀሪያ 🇩🇿
🇨🇴 ኮሎምቢያ ከ ጋና 🇬🇭 ይገናኛሉ

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰተደርገዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here