አፍሪካውያን ከዋክብት የዋንጫ ተጠባቂዋን እንግሊዝ ያስጨነቁበት ምሽትና ውጤቱ

0
14

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ የምድብ 12 ተጠባቂው ጨዋታ ያለ ግብ ተጠናቅቋል።

እንግሊዝ እና ጋና ያለ ግብ ነው የተለያዩት። ቡድኖቹ እኩል አራት ነጥብ ይዘው ወደ ጥሎ ማለፉ ለመጓዝ የመጨረሻዎቹን መርሐ ግብሮች ይጠብቃሉ።

ክሮሺያ ፓናማን 1 ለ 0 በማሸነፍ የመጀመሪያ ሦሥት ነጥብ አግኝታለች። የክሮሺያን ብቸኛ ግብ ቡዲሚር አስቆጥሯል።

ክሮሺያ ባገኘችው ሦሥት ነጥብ በጥሩ ሦሥተኝነት ወደ ጥሎ ማለፉ ለመሻገር ያላትን ተስፋ ከፍ ማድረግ ችላለች። የጨዋታ ውጤቱን ተከትሎ ፓናማ ከዓለም ዋንጫው ተሰናብታለች።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት

በከታች መጀመሪያው ኮመንት ላይ ያስቀመጥነውን ሊንክ በመንካት አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here