ባሕር ዳር: ሰኔ 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዓለም ዋንጫ የምድብ 9 ጨዋታ አልጄሪያ ጆርዳንን 2 ለ 1 በኾነ ውጤት አሸንፋለች።
ጆርዳን በ36ኛው ደቂቃ በኒዛር አል ራሽዳን ግብ ቀዳሚ መኾን የቻለች ቢኾንም ከእረፍት መልስ የአፍሪካ ወኪል አልጄሪያ በ69ኛው ደቂቃ በናዚም ቤንቡአሊ እና በ82ኛው ደቂቃ በአሚን ጉኢሪ ግቦች ጨዋታውን በበላይነት አጠናቃለች።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



