ለሊት የተካሄዱ ጨዋታዎች ውጤት

0
26
ባሕር ዳር ፡ ሰኔ 16/2018ዓ.ም(አሚኮ) በዓለም ዋንጫ የምድብ 2ኛ ጨዋታ ፈረንሳይ ኢራቅን 3ለ0 በማሸነፍ ወደ ጥሎ ማለፉ ተቀላቅላለች። በዚህ ጨዋታ ኪሊያን ምፓፔ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ደንበሌ ሦሥተኛዋን ግብ አስቆጥሯል።
ኖሮዌይ ደግሞ ሴኔጋልን 3 ለ 2 ረታለች።
የኖርዌይን የማሸነፊያ ግቦችን ሁለቱን ሀላንድ ሲያስቆጥር ሦሥተኛዋን ፔደርሰን አስቆጥሯል። ኖርወይ በዚህ ምድብ 6 ነጥብ በማግኘት ፈረንሳይን ተከትላ ወደ ጥሎ ማለፉ ተቀላቅላለች።
የሴኔጋልን ከሽነፈት ያልታደጉ ሁለት ግቦች ሳአር አስቆጥሯል።
ሴኔጋል በጥሩ ሦስተኝነት ወደ ጥሎ ማለፍ የሚያሻግራትን ጠባብ ዕድል ለመሞከር ከኢራቅ ጋር የምታደርገውን የመጨረሻ ጨዋታ ትጠብቃለች።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here