የፈረንሳይ እና የሴኔጋል ፍልሚያ በዓለም ዋንጫው !

0
157

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የምድብ መክፈቻ ጨዋታ ፈረንሳይ አና ሴኔጋል በኒው ጀርሲው ሜትላይፍ ስታዲየም ጨዋታቸውን ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ ያደርጋሉ።

ይህ ታሪካዊ ፍልሚያ ከ24 ዓመታት በፊት ሴኔጋል በ2002 ዓለም ዋንጫ ላይ ፈረንሳይን 1-0 ያሸነፈችበት ጨዋታ ትዝታን የቀሰቀሰ በመኾኑ በጉጉት እየተጠበቀ ነው።

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ዲዲየር ዴሻምፕ እጅግ ጠንካራ እና ጥልቀት ያለውን ስብስባቸውን ይዘው ወደ ሜዳ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጉልበት ህመም ላይ የነበረው ተከላካዩ ዊሊያም ሳሊባ አገግሞ በቋሚነት ይሰለፋል ተብሎ ሲጠበቅ በኪሊያን ምባፔ፣ ኡስማን ዴምቤሌ እና ማክል ኦሊሴ የሚመራው አስፈሪ የፊት መስመር ሴኔጋል ላይ በቀላሉ ግብ እንደሚያስቆጥር ይገመታል።

በፓፔ ቲያው የሚመራው የሴኔጋል ስብስብ አንጋፋውን ግብ ጠባቂ ኤዱዋርድ ሜንዲ እና ካሊዱ ኩሊባሊ የተከላካይ መስመር ላይ እንሚያሰልፍ ሲጠበቅ በፊት መስመር ላይ ደግሞ ሳዲዮ ማኔ፣ ኒኮላስ ጃክሰን እና ኢሊማን ንዲያዬ የፈረንሳይን ተከላካዮች እንደሚፈትኑ ይጠበቃል።

በሳሙኤል ጥሩነህ (ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአሚኮ የተግባር ተማሪ)

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here