ባሕር ዳር: ግንቦት 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከበርንሌይ የሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ ይጠበቃል።
መድፈኞቹ በ79 ነጥብ የሊጉ መሪ በመኾን ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ። ጨዋታውን ካሸነፉ ከተከታያቸው ማንቸስተር ሲቲ ጋር ያላቸውን ልዩነት ለጊዜው ወደ አምስት ነጥብ ከፍ የሚያደርጉ ይኾናል።
በርንሌይ በበኩሉ በ21 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲኾን ቀደም ብሎ ወደ ሻምፒዮን ሺፕ መውረዱ ይታወሳል።
የምሽቱ ጨዋታ ለሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት እያደረገ ለሚገኘው ታሪካዊ ጉዞ እጅግ ወሳኝ እና የመጨረሻ ደረጃ ላይ የደረሰ መርሐ ግብር ነው።
ከተከታዩ ማንቸስተር ሲቲ በሁለት ነጥብ ብቻ እርቆ እና በግብ ተበልጦ ለሻምፒዮንነት እየተጫወተ የሚገኘው አርሰናል የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ገብቶ ወደ ሜዳ ይገባል።
በርንሌይ በበኩሉ መውረዱን ያረጋገጠ ቡድን በመኾኑ ወደ ሜዳ የሚገባው ያለምንም ተጽዕኖ ነው። ይህም ለአርሰናል ከፍተኛ ጫና እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
ጨዋታው ምሽት 4:00 ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል።
ውድ የገጻችን ተከታዮች አጓጊው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሊጠናቀቅ ጫፍ ላይ ደርሷል። ዕውን አርሰናል ቀሪ ጨዋታዎችን አሸንፎ ሻምፒዮን መኾኑን ያረጋግጥ ይኾን ወይስ ሌላ ተዓምር ይፈጠር ይኾን ?
ግምታችሁን አጋሩን?
ዘጋቢ፦አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



