ኢትዮጵያ እና ግብጽ አቻ ተለያዩ።

0
18

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ እየተሳተፈ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመክፈቻ ጨዋታው ከግብጽ አቻው ጋር ተገናኝቶ ያለግብ አቻ ተለያይቷል።

ከ22 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ በዚህ ታላቅ አሕጉራዊ መድረክ ላይ ተሳትፎ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጠንካራ ፉክክር አድርጓል።

ብሔራዊ ቡድኑ በምድብ አንድ ከሞሮኮ፣ ከግብጽ እና ከቱኒዚያ ጋር ነው የተደለደለው።

በዘንድሮው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ 16 የአሕጉሪቱ ሀገራት የሚሳተፉ ሲኾን በውድድሩ ጥሩ ውጤት የሚያስመዘግቡ 10 ሀገራት በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ የማለፍ ዕድል የሚያገኙ ይኾናል።

ብሔራዊ ቡድኑም በቆይታው ይህን ግብ ለማሳካት የሚጫዎት ይኾናል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here