ባሕር ዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር ዛሬ ይጫወታሉ።

0
36

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 31ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል ባሕር ዳር ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ አንዱ ነው።

በ30ኛ ሳምንት ጨዋታው ፋሲል ከነማን ያሸነፈው ባሕር ዳር ከተማ በጥሩ የማሸነፍ ሥነ ልቦና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ ይገባል።

በአንጻሩ በነገሌ አርሲ ሽንፈት የገጠመው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ወደ ማሸነፍ ለመመለስ የሚጫዎት በመኾኑ የተሻለ ፉክክር የሚታይበት ጨዋታ ይኾናል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

የጣና ሞገዶቹ በሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ በ40 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲኾን ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በ35 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኙት።

ጨዋታውም በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒበርሲቲ ስታዲየም ቀን 10፡00 ላይ ይካሄዳል።

ሌላው ጨዋታ ፋሲል ከነማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ነው።

ፋሲል ከነማ ባለፈው የሊጉ ሳምንት በጣና ሞገዶቹ ሸንፈት የገጠመው ሲኾን ዛሬ ወደ አሸናፊነት ለመምጣት ነው የሚጫወተው።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በበኩሉ ባለፈው ሳምንት በምድረ ገነት ሽረ ሸንፈት የገጠመው ሲኾን ዛሬ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ነው ጨዋታውን የሚያደርገው።

ሁለቱም ክለቦች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚጫዎቱ በመኾኑ የተሻለ ፉክክር የሚታይበት ጨዋታ ይኾናል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ፋሲል ከነማ በሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ በ43 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በበኩሉ በሊጉ በ42 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው።

የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ደረጃቸውን ለማሻሻል ስለሚያግዛቸው ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጨዋታውም በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒበርሲቲ ስታዲየም ምሽት 12፡00 ላይ ይካሄዳል።

በሌላ የሊጉ ጨዋታ ሸገር ከተማ ከሲዳማ ቡና ቀን 7፡00 ላይ እና አርባ ምንጭ ከተማ ከወላይታ ዲቻ ደግሞ ቀን 10፡00 ላይ በአዲስ አበባ አበበ ቢቄላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here