ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 29ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ ሲጠናቀቅ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል ባሕር ዳር ከተማ ከምድረ ገነት ሽረ 10:00 ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ባሕር ዳር ከተማ በሊጉ 28 ጨዋታዎችን አድርጎ በ36 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው።
በአንጻሩ ተጋጣሚው ምድረ ገነት ሽረ በ29 ነጥብ ከደረጃ ሠንጠረዡ ግርጌ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ 18ኛ ደረጃ ላይ ነው የተቀመጠው።
ባሕር ዳር ከተማ ባለፈው የሊጉ ሳምንት ጨዋታ ከሸገር ከተማ ጋር ተገናኝቶ 2ለ0 የተሸነፈ ሲኾን ዛሬ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫዎታል።
ተጋጣሚው ምድረ ገነት ሽረ በበኩሉ ባለፈው ሳምንት ከወላይታ ዲቻ ጋር የነበረውን ጨዋታ 1ለ0 መሸነፉ ይታወሳል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሲዳማ ቡና 8፡00 ላይ በአዲስ አበባ አበበ ቢቄላ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ሌላው በሊጉ የሚካሄድ ጨዋታ ነው።
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !



