ባሕር ዳር: ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የመጀመሪያ ዙር የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ አትሌቲኮ ማድሪድ በሜዳው ሪያድ ኤር ሜትሮ ፖሊታኖ አርሰናልን ምሽት 4:00 ላይ ያስተናግዳል።
አትሌትኮ ማድሪድ በአውሮፓ መድረክ በሜዳው በእንግሊዝ ቡድኖች ተሸንፎ አያውቅም።
በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጠንካራ አቋምን እያሳየ የሚገኘው የእንግሊዙ ኃያል ክለብ አርሰናል ለዋንጫ በሚያደርገው ግስጋሴ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።
መድፈኞቹ በታሪክ አንስተውት የማያውቁትን የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ለማንሳት በሚያደርጉት ግስጋሴ የአትሌቲኮን ግንብ ማፍረስ ይጠበቅባቸዋል።
በአትሌቲኮ ማድሪድ ተከላካዩ ፓብሎ ባሪዮስ፣ ዴቢድ ሄንኮ እና ኒኮ ጎንዛሌዝ በጉዳት ምክንያት ከጭዋታው ውጭ መኾናቸው ተረጋግጧል።
ኤልሞራ ሉክማን ጨምሮ ወሳኝ ተጫዎቾቹ የመሰለፍ ዕድላቸው አጠራጣሪ እንደኾነም ተነስቷል።
በአርሰናል በኩል ማርቲን ኦዲጋርድ እና ሪካርዶ ካላፊወሪ በጭዋታው የሚሰለፉ ሲኾን ካይ ሀበርትዝ እና ቲምቨር ደግሞ ከጭዋታ ውጭ መኾናቸው ታውቋል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !



