ባሕር ዳር: ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና ቁልፍ ተጫዋቾቻቸውን በጉዳት አጥተዋል። ላሚን ያማል በባርሴሎና በኩል የግራ እግር ጡንቻ መሳሳብ ሲገጥመው፤ በሪያል ማድሪድ በኩል ደግሞ አርዳ ጉለር የቀኝ እግር ጡንቻ መሳሳብ ጉዳት ገጥሞታል።

ተጫዋቾቹ የገጠማቸው ጉዳት ለማገገም ሳምንታትን እንደሚወስድ ሲገለጽ ለቀሪ የውድድር ዓመቱ ጨዋታዎች እንደማይመለሱ ክለቦቹ አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተጫዋቾች እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን ግንቦት 10 በሚካሄደው የኤልክላሲኮ ግጥሚያ የመድረስ ዕድላቸው እጅግ አነስተኛ እንደኾነ ተገልጿል።
በተጨማሪም የሪያል ማድሪዱ ተከላካይ ኤደር ሚልታኦ ባጋጠመው ጉዳት ከውድድር ዓመቱ ውጭ መኾኑ ተነግሯል።
ተጫዋቾቹ ከጉዳታቸው አገግመው ለመጭው የዓለም ዋንጫም ለመድረስ ከፍተኛ ክትትል እንደሚጠይቃቸው ኢኤስፒኤን ዘግቧል።
በአድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



